እኛ ማን ነን
የኢትዮጵያ ፈርኒቸር አምራቾች ኢንዱስትሪ ማህበር
ማህበሩ በኢትዮጵያ ላሉ በፈርኒቸርና ተያያዥ ምርቶች ዙሪያ ለሚሰሩ አምራቾች የመጀመሪያዉ ብቸኛ ማህበርና የአምራቾች ወኪል በመሆን እያገለገለ ነዉ፡፡ የማህበሩ አባል ሆነዋል? አባል ሆነዉ ከማህበሩ ጋር አብሮ በመስራት ስራዎን ያቅሉ ለስራዎ አስፈላጊ የሆኑ ነጻ የምክር አገልግሎቶችን በነጻ በማንኛዉም ጊዜ ያለገደብ ያግኙ ጉዳዮን በተቀላጠፈ ሁኔታ ለማሰራት ለማሀበሩ ይስጡ፤ እርስዎ በዋናዉ በስራዎት ላይ ያተኩሩ ማህበሩ የመረጃ ዋነኛ እና ቀዳሚ ምንጭዎ ነው
አላማዎች
1. የፈርኒቸር ኢንዱስትሪዉ በመንግስት የፖሊሲ ዝግጅት ዉስጥ ቅድሚያ ቦታ እንዲያገኝ እና በአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ዉስጥ የመጀመሪያዉን ድርሻ እንዲያበረክት ማድረግ
2. በፈርኒቸር ኢንዱሪዉ የንግድ ለንግድ ትስስሩ ወደ ቀጣይ ደረጃ እንዲደርስ ማድረግ
3. በኢነዱስትሪዉ ዘርፍ በተሰማሩ አባት መካከል አወንታዊ የጋራ ትስስር ሁኔታን መፍጠር
4. በሀገር ዉስጥ ያሉ ፈርኒቸር በማምረት ዘርፍ ላይ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች ምርቶቻቸዉን በሀገር ዉስጥና በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ አባላት በተወሰኑ ምርቶች ላይ እንዲያተኩሩ ማገዝ፤
5. በዘርፉ የተሰማሩ ኢንዱስትሪዎች የተሸሻሉ የቴክኖሎጂ ማድረግ፤ ዉጤቶችን ተጠቃሚ እንዲሆኑ ማድረግ፤
6. ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ መድረክ በመፍጠር ማድረግ፤ ለችግሮቹ ዘላቂ መፍትሄ እንዲያኙ ማድረግ፤
7. በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ከዉጪ ሀገር የሚገቡ ፈርኒቸሮች በብቃት እንዲያመርቱ እና እንዲተኩ በማድርግ ለሀገሪቱ የዉጪ ምንዛሪን ለማዳን ማስቻል፤
8. ኢንዱስትሪዉ በሰለጠነ የሰዉ ሃይል እና ቴክኖሎጂ እንዲዳብር ከትምህርት ተቋማት ጋር በመተባባር አስተዋጽኦ ማድረግ፤
9. መጥነት ያለዉ የፈርኒቸር የቴክኒክ መስፈርቶች እንዲኖር እና በስራ ላይ እዲዉል ድጋፍ ማድረግ